Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ለ1ሺህ 580 እስረኞች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ለ1ሺህ 580 እስረኞች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የደቡብ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሶፎኒያስ ደስታ በሰጡት መግለጫ÷ 1ሺህ 443ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለ1ሺህ 580 እስረኞች ይቅርታ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በይቅርታ አሰጣጥ ስነ ስርዓት አዋጅ ቁጥር 157/2007 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 141/2008 እና በመመሪያ ቁጥር 6/2008 መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጠውን ይቅርታ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ይቅርታ መሰጠቱን አመላክተዋል፡፡
በአጠቃላይ ለ1ሺህ 580 እስረኞች የይቅርታው ተጠቃሚ መሆናቸው ጠቁመው÷ ከእነዚህ መካከል ሙሉ ይቅርታ የተደረገላቸው 1ሺ 502 ወንዶች እና 78 ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ ከዕድሜ ልክ እስራት ወደ 25 ዓመት ዝቅ የተደረገላቸው 13 ወንዶች መሆናቸውንም አብራርተዋል።
በተፈረደባቸው ወንጀል ግማሽ የታሰሩ እንዲሁም የፍርድ ጊዜያቸውን በሁለት ሦስተኛ ያጠናቀቁ፣ በማረሚያ ቆይታቸው በስነ ምግባራቸው የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ የይቅርታው ተጠቃሚ መሆናቸውንም ኃላፊው አስረድተዋል።
እርቅ ፈጽመው ካሳ የከፈሉና በጥፋታቸው የተጸጸቱ እንዲሁም የጎዱትን ማህበረሰብ ለመካስ የተዘጋጁትንም ያካትታል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.