Fana: At a Speed of Life!

20 የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የምግብ፣ የእህል ዘሮች፣ የሕክምና አቅርቦቶችንና የውሃ ማከሚያ ቁሳቁሶችን የያዙ 20 ተሽከርካሪዎች ትናንት መቀሌ መግባታቸውን አስታውቋል።
የሕክምና አቅርቦቱ በትግራይ ክልል የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ 13 የጤና ጣቢያዎች ለሚገኙ 65 ሺህ ታካሚዎች ለሶስት ወር እንዲሁም በአራት ሆስፒታሎች ለሚገኙ 6 ሺህ 600 የስኳር ሕሙማን ለአንድ ወር እንደሚያገለግል ተመላክቷል፡፡
የሰብአዊ እርዳታው በሽሬ፣ ሰሜና እና ሽራሮ ሆስፒታሎች ለሚገኙ የጤና አገልግሎት ስራ አቅም እንደሚያሳድግ እንዲሁም እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ 19 የጤና ማዕከላት 20 ሺህ ታካሚዎችን ጨምሮ የጤና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸውን ለአንድ ወር የሚያገለግል የምግብ ድጋፍ ያካተተ መሆኑንም ነው ኮሚቴው የገለጸው፡፡
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድጋፍ በመቀሌ፣ አዲግራት፣ ሽሬ፣ አድዋና አክሱም ከተሞች የሚገኙ የውሃ መሰረተ ልማቶችን በመጠገንና በማከም በከተሞቹ የሚኖሩ ዜጎች የንጹህ ውሃ መጠጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ብሏል።
የውሃ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ በአይደር ሆስፒታል ሕክምናቸውን የሚከታተሉ 500 ዜጎች ንጹህ መጠጥ እንዲያገኙ ያደርጋል ያለው ኮሚቴው÷ የሽሬ ሆስፒታል ሕንጻ ዳግም ስራ መጀመር በየቀኑ 100 ታካሚዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አመልክቷል።
በድጋፉ አማካኝነት በትግራይ ክልል ገጠራማ አካባቢዎች የሚተከሉት የውሃ ፓምፖች 40 ሺህ ዜጎችን ተደራሽ እንደሚያደርግ ነው ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
ከሕክምና እና የውሃ አቅርቦት ድጋፍ በተጨማሪ ለ15 ሺህ ዜጎች የሚያገለግሉ የቤት ውስጥ እቃዎችና 20 ሺህ አርሶ አደሮች የሚሰራጩ የእህል ዘሮች መካተቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.