Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል- የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘከርያ በሰጡት መግለጫ÷ ሕዝበ ሙስሊሙ 1ሺህ 443ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያከብር ፖሊስ በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግብረ ኃይል አቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አመልክተዋል።
ምዕመናኑ ሶላት ወደሚያደርጉበት ስፍራ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ዋና ዋና መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑና አማራጭ መንገዶች ደግሞ ለተሽከርካሪ ክፍት እንደሚደረጉም አንስተዋል፡፡
ሆኖም በክልሉ አንድ አንድ ሰላም የማይፈልጉና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ግጭት ለማስነሳት የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳሉ የጠቆሙት ኮሚሽነር ነስሪ÷ይህ ዓይነት ድርጊት ሲያጋጥም ህብረተሰቡ ማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ህብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር እያከናወነ የሚገኘውን ሰላም የማስከበር ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.