Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቃዮች እና አቅመ ደካሞች ለዒድ አል ፈጥር በዓል መዋያ ስጦታ እየተበረከተ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተፈናቃዮች እና አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡
 
የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጦርት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በአይሳኢታና ዱብቲ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
ድጋፋ በዱብቲ መጠለያ የሚገኙ 1 ሺህ በላይ አባወራና እማወራዎችን ያካተተ ሲሆን÷ ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም ዱቄት እና 5 ሊትር የምግብ ዘይት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 
በተመሳሳይ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማሕበር የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በከሚሴ ከተማ ለ400 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ማዕድ አጋርተዋል።
 
የማሕበሩ አስተባባሪ መሀመድ ጁድ ዒድን ከቤት ወጥተው የሰው ፊት ሳያዩ በቤታቸው በደስታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያሳልፉ ዘንድ በማህበራዊ ሚድያ ገንዘን በማሰባሰብ ከ200 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ 4 ግመሎችን በመግዛት በከተማው ከሁሉም ቀበሌ ለተውጣጡ ለ400 አቅመ ደካማ ወገኖች ማበርከታቸውን ገልፀዋል።
 
ከዚህ ቀደም “ረመዳንን ከሚስኪኖች ጋር” በሚል መሪ ሀሳብ ለ400 አባወራዎች ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለረመዳን የአንድ ወር አሰቤዛ ድጋፍ ማድረጋቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.