በጎንደር የአዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ወጣቶች ለኢድ አልፈጥር በዓል በመስጊድ የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ነገ የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ሶላት በሚካሄድበት የመስጊድ ግቢ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል ።
የጽዳት ዘመቻውን ያካሄዱት ከእስልምና እና ከክርስትና ሐይማኖቶች የተወጣጡ ወጣቶች በኮሚቴ በመደራጀት ነው፡፡
ከጽዳት ዘመቻው ተሳታፊዎች መካከል ፈንታሁን አደም እና አያሌው ህብረት እንደተናገሩት÷ ሁለቱም ሐይማኖቶች ለዘመናት ተቻችለው እና ተከባብረው አብረው የሚኖሩ ናቸው፤ ይህንን ለማስቀጠልም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
የትኛውም ፅንፈኛ አክራሪ ሃይል እምነትን መደበቂያ አድርጎ በእምነቶች መካከል ግጭት እንዲፈጥር አንፈቅድም ነው ያሉት ወጣቶቹ።
የአዘዞ ጠዳ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳለው ካሳ በበኩላቸው÷ በሁለቱ እምነቶች መካከል የነበረው የቆየ አብሮነት በፅንፈኞች ሴራ መቼም ቢሆን አይሻክረም ብለዋል።
ወጣቶች በኢድ መከበሪያ ቦታ የፅዳት ዘመቻ ማካሄዳቸው ትናንት የነበረው የሃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር አሁንም መቀጠሉን ያሳይል ሲሉም ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡
በአበራ መኮነን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡