Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ዋለ።

ታላቁን የረመዳን ወር ለ30 ቀናት ዱኣ በማድረግ፣ በሰላት እና ጾም በመጾም ያሳለፈው ህዝበ ሙስሊሙ የጾም መገባደጃ ምልክት የሆነችው ጨረቃ መታየቷን ተከትሎ ዛሬ ኢድ አልፈጥርን በተለያዩ ሁነቶች አክብሯል።

በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም ነው በዓሉ የተከበረው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ እና ከዚያም በኋላ ከቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤቶቻቸው ጋር በመሆን በዓሉን አክብረዋል፡፡

በተለይም በአዲስ አበባ ስታድየም የዕምነቱ ተከታዮች በኢድ ሰላት አክብረውታል።

ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪ ጋር በተያያዘ ከተዘጋጁ መርሀ ግብሮች መካከል አንዱ በሆነው ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ ላይ ለመታደምም የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንዳሉትም ፥ ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያዳበራቸውን መልካም ስራዎች ከረመዳን ውጪ ባሉት ወራትም የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስና የተቸገሩትን በመርዳት እንዲሁም የማዕድ ማጋራቱን ስራ በቀጣይነት በመፈፀም ከፈጣሪው የሚያገኘውን ምንዳ ከፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.