የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከዛሬ ጀምሮ የተለያዩ የፀጥታ ተቋማትና ልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ

By Meseret Awoke

May 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከዛሬ ጀምሮ የተለያዩ የፀጥታ ተቋማት እና ልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ።

እስከ እሁድ በሚቆየው የጉብኝት መርሃ ግብር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ ዜጎች ይሳተፋሉ።

ጉብኝቱም በተቋማቱ እና የልማት ፕሮጀክቶቹ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና የመከላከያ ጀነራሎችን ያካተተ ቡድን በተቋማቱና የልማት ፕሮጀክቶቹ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።