Fana: At a Speed of Life!

ሰላም በተግባር እና በሁሉም ተሳትፎ ይመጣል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ በአዲስ አበባ ስቴዲየም እየተከበረ በሚገኘው የ1 ሺህ 443 ዓመተ ሂጅራ የዒድ አልፈጥር በዓል ተገኝተው መልክት አስተላልፈዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪ ጋር በተያያዘ ከተዘጋጁ መርሀ ግብሮች መካከል አንዱ በሆነው ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡ የጎረቤት ሀገራት የእስልምና ተቋማት ተወካዮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና ለበዓሉም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ንግግራቸውን ጀምረዋል፡፡

ስለሰላም ባነሱት ሃሳብ ሰላም የሚመጣው በህዝብ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን ፥ “የሚመጣውም በተግባር ነው፤ ሰላም የሚመጣው በህዝብ ነው፤ ሰላም የሚመጣው በመንግስት ነው ፤ በተለዩ ሰዎች ብቻ ሰላም ሊመጣ አይችልም” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

ይህንንም በማወቅ ወደ ሰላም፣ ወደ ልማት ልንመለስ ይገባልም ብለዋል ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፡፡

አክለውም የንጹሃን ደም አይፍሰስ፣ ሰዎች አይፈናቀሉ፣ አንዱ አንዱን አይዝረፍ ያሉ ሲሆን፥ ይህን ተግባር በመተው ወደሰላም እንመለስ ሲሉም መክረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.