የኢድ አልፈጥር በዓል በሐረር ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 24፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሐረሪ ከተማ ተከብሯል።
በሰላት ስነስርዓቱ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝብ ሙስሊሞች በተገኙበት በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም ተከናውኗል፡፡
በሰላት ስነ ስርአቱ የተሳተፉ የእምነቱ ተከታዮች የኢድ በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመረዳትና በአብሮነት ሊሆን እንደሚገባ ገልጸው ህዝብ ሙስሊሙ ለሠላምና ለሃገር አንድነት ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ኢድ ሲከበርም በረመዳን ጾም ወቅት የነበረው መተጋገዝና መደጋገፍ ከዚህ በኋላም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ ተላልፏል።
የኢድ ሰላቱን የሀረር ጀምዐ መስጊድ ኢማም ሼክ ሙክታር ሙባሪክ የመሩት ሲሆን፥ የሁጥባ ስነ ስርአትም ተካሂዷል፡፡
በተሾመ ኃይሉ