Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከኢድ ሰላት ምዕመኑ ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የኢድ ሰላት ከመሰገዱ በፊት በሰማዕታት ሀውልት አካባቢ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።

ምዕመኑ አሁን ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ በመረጋጋት ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በቀጣይ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ መግለጹን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።

ምዕመኑ አሁን ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ በመረጋጋት ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በቀጣይ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ መግለጹን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.