Fana: At a Speed of Life!

በ3 በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 146 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ ሦስት በረራዎች ከሳዑዲ አረቢያ 1ሺህ 146 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የማስመለሱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ሲሆን፥ ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ወደ ትውልድ አገራቸው በሶስት በረራዎች 1 ሺህ 146 ዜጎች ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 802 ወንዶች፣ 203 ሴቶች እና 41 ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡

አዲስ አበባ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡

መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.