Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የኢድ አል ፈጥር በዓልን ከተፈናቃዮች ጋር አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ምክንያት ከኪልበቲ ረሱ ተፈናቅለው በመጠለያ ከሚገኙ ወገኖች ጋር ዒድ አል ፈጥርን አክበረዋል፡፡

1443ኛው ሂጅራ ኢድ አልፈጥር በዓል በአፋር ክልል ተከብሯል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግም የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በአሸባሪው ህወሃት ምክንያት ከኪልበቲ ረሱ የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር በጋራ አክብረዋል፡፡

በተመሳሳይም የክልሉ ክፍተኛ አመራሮች በሠመራ፣ ሎጊያ፣ ዱብቲ፣ አይሰኢታ፣ ጉያህና ሌሎች አካባቢዎች ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮቾ ጋር በዓሉን በጋራ አክብረዋል፡፡

1 ሺህ 443ኛው ሂጅራ ኢድ አልፈጥር በዓል በአፋር የተከበረ ሲሆን፥ በሰመራ ስታዲየም ከኪልበቲ ረሱ የተፈናቀሉ ከ1 ሺህ በላይ ወገኖች መታደማቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.