Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሊገናኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን ጋር በዚህ ሳምንት በቱርክ ሊገናኙ መሆኑ ተሰማ፡፡

መሪዎቹ በቱርክ ተገናኝተው በወቅታዊና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ።

በሩሲያ- ዩክሬን ያለውን ውጥረት ለማርገብ የሚያግዝ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድ በሚቻልበት አግባብ ላይ እንደሚመክሩም ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በቱርክ ኢስታንቡል በፈረንጆች መጋቢት 29 በሩሲያ እና በዩክሬን ልዑካን መካከል ተደርጎ የነበረው ውይይት ጦርነቱን ለማስቆም በተደረገው የድርድር ሂደት ውስጥ እንደ ትልቅ ስኬት ይቆጠራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.