Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በድሬዳዋ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

በበዓሉ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር÷ ህዝበ ሙስሊሙ ለሠላም መረጋገጥ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

እስልምና ሰላምን እንደሚሰብክ ጠቅሰው÷ በአስተዳደሩ ቀጣይነት ያለው ሰላም እንዲረጋገጥ ህዝበ ሙስሊሙ የማይሻር ሚናውን መወጣት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የድሬዳዋ የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዚዳንት ሼህ መሀመድ አብደላ በበኩላቸው፥ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ወደ ኢድ ሰላት መስገጃ ስፍራ አምርተው የስግደት መርሀ-ግብር መከናወኑን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.