በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ሲያሸንፍ አዲስ አበባ ከሃድያ ሆሳዕና አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከሃድያ ሆሳዕና ተጫውተዋል።
ጨዋታው ሶስት አቻ በሆነ ውጤት ሲጠናቀቅ አዲስ አበባ ከተማ ሶስት ጊዜ መምራት ችሎ ነበር።
ለአዲስ አበባ ከተማ ሪችሞንድ ኦዶንጎ አንድ እንዲሁም አቤል ነጋሽ ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ሳምሶን ጥላሁን፣ ሀብታሙ ታደሰ እና ኤፍሬም ዘካርያስ ደግሞ ለሃድያ ሆሳዕና ጎሎቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
ማምሻውን በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ ወላይታ ዲቻን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ጨዋታውን ወላይታ ዲቻ 1 ለ 0 መምራት ቢችልም፥ ፋሲል ከነማ መልካሙ ቦጋለ በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም በረከት ደስታ እና ኦኪኪ አፎላቢ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 3 ለ 1 አሸንፎ ወጥቷል።
የወላይታ ዲቻን ማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ በረከት ወልደዮሐንስ አስቆጥሯል።