Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሳህል ቀጠና የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አፍሪካ ሳህል ቀጠና የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች ተባብሰው መቀጠላቸውን የተባበሩት መንግስት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገልጸዋል፡፡
 
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በምዕራፍ አፍሪካ በሚገኙ ሶስት አገራት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ኒጀር ኒያሚ ገብተዋል፡፡
 
ጉተሬዝ ከኒጀር ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ባዞም ጋር ባደረጉት ውይይት÷ሽብርተኝነት የአፍሪካ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እየፈተነ የሚገኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በዚህም በተለያዩ አገራት በሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች በርካታ ንጹሃን ሲገደሉ፥ በሚሊየን የሚቆጠሩት ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
 
ድርጊቱ አሁን ላይ በተለይም በአፍሪካ ሳህል ቀጠና አገራት ተባብሶ መቀጠሉን ነው ዋና ጸሃፊው የተናገሩት፡፡
 
ስለሆነም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሽብርተኝት የሚያስከትለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በመገንዘብ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ነው ያሉት፡፡
 
የመንግስታቱ ድርጅት ለሳህል ቀጠና አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ያሉት ዋና ጸዋፊው÷ለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
 
በምዕራብ አፍሪካ ሳህል ቀጠና ቦካ ሃራም እና ኤስ የተሰኙ የሽብር ቡድኖች እንዲሁም ሌሎች ጽንፈኛ ጂሃዲስት ቡድኖች በስፋት እንደሚንቀሳቀሱ ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.