Fana: At a Speed of Life!

የማሊ ወታደራዊ መንግስት ከፈረንሳይ ጋር ያደረገውን ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሊ ወታደራዊ መንግስት ከፈረንሳይ ጋር ያደረገውን ወታደራዊ ስምምነት ማቋረጡን አስታወቀ፡፡

የወታደራዊው መንግስት ቃል አቀባይ አብዱላይ ማይጋ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ የማሊ ሪፐብሊክ ከቀድሞ ቅኝ ገዥ ፈረንሳይ ጋር ያደረገው ወታደራዊ ስምምነት መስመሩን በመሳቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የፈረንይ እና የማሊ ሪፐብሊክ ኃይሎች በሰሀል ቀጠና በጋራ ሲያደርጉ የነበረው ወታደራዊ ዘመቻም በፈረንጆቹ ሰኔ 2021 እንዲቆም መወሰኑንም ቃል አቀባዩ አስታውሰዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2020 በቀጠናው የሚንቀሳቀሰውን የሃይማኖት አክራሪ ቡድን ጥቃት ለማስቆም በማሊ ወታደራዊ መንግስት እና በፈረንሳይ መንግስት መካከል ስምምነት መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጅ የፈረንሳይ ኃይሎች በተደጋጋሚ የማሊን የአየር ክልልጥሰው መግባታቸው ለወታደራዊ ስምምነቱ መቋረጥ እንደምክንያትንት መጠቀሱን ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡

የተቋረጠው ወታደራዊ ስምምነት ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ ፈረንሳይ በማሊ ሪፐብሊክ ላይ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት እልባት የሚሰጥ ነው መባሉን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.