Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የ15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ15 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ከድጋፉ መካከል÷ 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያህሉ የአይነት ሲሆን 7 ሚሊየኑ ደግሞ በገንዘብ መልክ የተደረገ ነው፡፡
የገንዝብ ድጋፉን የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል።
አቶ ጂማ ዲልቦ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ በአጭር ጊዜ 250 ለሚጠጉ ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥሪ በማድረግ ከ430 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
በዚህም በአማራ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ300 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እንዲሁም 6 ሚሊየን ብር ደግሞ በገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ለአፋር ክልል 100 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነትና 4 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ በቀጣይም እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተቋቁሞ ለማለፍ በ”ቡሳ ጎኖፋ” የኦሮሞ የመረዳዳት ባህል አሰራር መሰረት ከሲቪክ ማህበረሰብ ጋር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.