Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለዩክሬን የላከቻቸው የጦር መሳሪያዎች ዓይነትና መጠን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን የላከቻቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ዓይነት እና መጠን ይፋ መሆኑ ተሰማ።

ባለፈው ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ቃል ከገቡት የጦር መሳሪያ እርዳታ ውስጥ 80 በመቶ ያህሉ የኤም- 777 መድፎች እና ጥይቶች ኬቭ መድረሳቸው ተገለጿል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ ፀረ-አውሮፕላን ራዳሮችን እና 5 ሺህ ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ማቅረቧ ተመልክቷል።

ቀደም ሲል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን 18 መድፎች ብቻ ለማቅረብ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም የመድፎችን ቁጥር ወደ 90 ከማሳደጋቸውም በላይ 155 ሚ.ሜ ጥይቶች ፣ አስር ፀረ-መድፍ ራዳሮች ፣ ሁለት ለዓየር ስለላ የሚውሉ ራዳሮች፣ 200 ኤም-113 የሰራዊት ማጓጓዣዎች ፣11 ኤምአይ -17 ሄሊኮፕተሮች እና ሌሎች ወታደራዊ መሳሪያዎችን ለኬቭ ለማቅረብ መወሰናቸው ነው የተገለጸው፡፡

አሜሪካ ለዩክሬን ለማቅረብ ካቀደችው 155 ሚሜ ጥይቶች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ፣72 መድፎችእና አብዛኛዎቹ ራዳሮች ኬቭ መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን፥ የተቀሩትም በመጓጓዝ ላይ እንደሆኑ አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ መከላከያ ባለሥልጣን ዋሽንግተን ለዩክሬን ስላቀረበችው ወታደራዊ እርዳታ በፔንታጎን ለጋዜጠኞች ባብራሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ከጦር መሳሪያ አቅርቦቱ በተጨማሪም የዩክሬን ወታደሮች በጀርመን የኤም- 777 መድፍ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ እንደሆነ የጠቆሙት ባለስልጣኑ፥ 170 ያህሉ ስልጠናውን ወስደው እንደጨረሱ እና 50 ያህሉ ደግሞ ስልጠናውን በማገባደድ ላይ መሆናቸው ተገልጿል ሲል አርቲ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው፥ ዩክሬን ከምዕራባውያን ሀገራት የተሰበሰቡ የጦር መሳሪያዎች ተከማችተውባቸዋል ተብሎ በሚገመቱ ቦታዎች ላይ ሩሲያ ጥቃት አድርሳለች።

በዚህም 1 ሺህ 246 ከባድ መሳሪያዎችን እና መጠኑ ያልተገለፀ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን ማውደሟ ተነግሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.