Fana: At a Speed of Life!

“ኢትዮጵያን ወደተሻለ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝ ነው” – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ወደተሻለ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ ከሰሞኑ በሃይማኖት ሽፋን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ሁከቶችና ወንጀሎች ላይ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የፌደራል ፖሊስ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር እያዋሉ እንደሚገኙ ገልጾ÷ ተጠርጣሪዎቹም ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል።
ለዜጎች በሰላም መኖር ስጋትን የሚፈጥሩ በሃገር ህልውና ላይም አደጋን የሚደቅኑ አካላት ላይ መንግስት መውሰድ የጀመረውን እርምጃ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
በዚህ ሂደት ለጽንፈኝነትና አክራሪ አመለካከት ቦታ እንደሌለው በተግባር ያረጋገጠው መላው ህዝብ÷ ከሰሞኑ እንደታየው ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠትና ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ያሳየውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መንግስት ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ያሳለፍነው ሣምንት የስቅለት፣ የፋሲካ፣ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር፣ የኢድ አልፈጥርና የፍቼ ጫምባላላ በዓላት እንዲሁም አለም አቀፍ የሰራተኞች ቀንን ያስተናገድንበት ጊዜ መሆኑን አገልግሎቱ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ወቅት በጎንደር ከተከሰተው አሳዛኝ ጥፋት እንዲሁም እሱን ተከትሎ በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከታየው ፍጹም ከኢትዮጵያዊነት ስነ ምግባር ያፈነገጠ ወንጀል ባሻገር በዓላቱ በመላ ሀገሪቱ በድምቀት መከበራቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል፡፡
በዚህም በዓላቱ ኢትዮጵያውያን በፈተና ውስጥ ይበልጥ የሚጸና የአብሮነት እሴት እንዳላቸው ያሳዩበትና የሀገርንም ገጽታ ለመገንባት ያስቻሉ ናቸውም ብሏል።
በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያሳተፉት እነዚህ በአላት ከሃይማኖታዊ አስተምህሮታቸው ርቀው የጥፋት ማስተናገጃ እንዲሆኑ ለማድረግና በኢትዮጵያውያን መካከል የተዘረጋውን የአብሮነት ገመድ ለመበጠስ ያቀዱ ወንጀለኞች ብዙ ጥፋትን ለማድረስ በብርቱ የሞከሩበትም ወቅት መሆኑንም አውስቷል።
ይህ ውጥናቸው ባሰቡት የጥፋት ልክና ባቀዱት የወንጀል ስፋት መጠን እንዳይሳካ ላደረጉት ኢትዮጵያውያን በሙሉ መንግስት ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።
በተመሳሳይ ሕዝብ የሰጣቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት በጠንካራ ቅንጅትና እስከ ህይወት መስዋዕትነት ድረስ በመክፈል የተወጡ መላው የጸጥታ አካላትና ተባባሪ ተቋማትም ምስጋና ይገባቸዋል ብሏል፡፡
ከሰሞኑም በሃይማኖት ሽፋን በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ሁከቶችና ወንጀሎች ላይ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የፌደራል ፖሊስ፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር እያዋሉ እንደሚገኙ ገልጾ÷ ተጠርጣሪዎቹም ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ ይደረጋል ብሏል።
በዚህ ሂደት ለጽንፈኝነትና አክራሪ አመለካከት ቦታ እንደሌለው በተግባር ያረጋገጠው መላው ህዝብ ከሰሞኑ እንደታየው ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠትና ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ያሳየውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መንግስት ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.