Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የ2015 በጀታቸውን እያቀረቡ የሚያስገመግሙበት ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ146 የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በተሰጣቸው የበጀት ጣራ መሰረት የ2015 በጀት ዓመት በጀታቸውን አቅርበው የበጀት ዝግጅታቸው የሚሰማበትና የሚገመገምበት የበጀት ሰሚ ፕሮግራም ተጀመረ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ዓመታዊ የበጀት ሰሚውን ፕሮግራም በመሩበት ወቅት እንደገለጹት፥ የፌዴራል መንግስት ተቋማት የመጪው በጀት ዓመት በጀታቸውን ሲያዘጋጁ የተሰጣቸውን የበጀት ጣሪያ ባገናዘበ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነና ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታሳቢ ባደረገ መልኩ መዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የፌዴራል ባለበጀት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የ2015 ዓመት በጀታቸውን ሲያቀርቡ የውስጥ አደረጃጀታቸውን ፈትሸው አሰራራቸውን ማዘመንና ወጪ ቁጠባን መሰረት ያደረገ የእቅድ አፈጻጸም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አመላክተዋል፡፡
የበጀት ሰሚው ፕሮግራም ሲጀመር የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ እና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት የ2015 በጀት ዓመት በጀታቸውን አቅርበው መገምገሙን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.