Fana: At a Speed of Life!

አሁን ካሉብን ዘርፈብዙ ኢኮሚያዊ እና ማህበራዊ ፈተናዎች ለመውጣት እንደ ህዝብ በሚያስተሳስሩን እሴቶች ላይ ማተኮር ይገባል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አሁን ካሉባት ዘርፈ ብዙ ኢኮሚያዊ እና ማህበራዊ ፈተናዎች ለመውጣት እንደ ህዝብ በሚያስተሳስሩን እሴቶች ላይ ማተኮር ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ።
 
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህርና የብዝሃነት ተመራማሪው ዶክተር ከይረዲን ተዘራ እና የሰላም ግንባታ እና ግጭት አፈታት ምሁር እና አማካሪ ዶክተር ገለታ ሲሜሶ÷ በተወሰኑ ሃይሎች ጎልተው እንዲወጡ የተፈለጉት እና የሃይማኖት ገጽታ የተሰጣቸው ግጭቶች የአገር ህልውና ፈተናዎች ናቸው ብለዋል።
 
በእንዲህ አይነት ወቅት ከጀርባ ያለውን የነገሮች አላማ እና አካሄድ መመርመር ወሳኝ መሆኑን ምሁራኑ አስረድተዋል፡፡
 
መሰል ችግሮችን እንደ ህዝብ ነባር አብሮ የመኖር እሴቶችን በማጠናከር ልንመክታቸው ይገባል ነው ያሉት ምሁራኑ።
 
እንደ ህዝብ ብቻ ሳይሆን እንደ አማኝ ማህበሰረብ ለራስ ሳይወግኑ ነባር እሴቶችን የሚሸረሽሩ ተግባራትን በግልጽ ማውገዝ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ህግን የጣሱ እና አገርን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጡ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን አሳልፎ መስጠትም ከህዝቡ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
አጥፊዎችን እና የጥፋት ቦታዎችን አስቀድሞ መለየት እንዲሁም ችግር ፈጣሪዎችን ለህግ ማቅረብ ደግሞ ከመንግስት የሚጠበቅ ነው ብለዋል ፡፡
 
 
በትዕግስት አብርሀም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.