Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በንግድ ድርጅት ውስጥ የተከማቸ የጦር መሣሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በንግድ ድርጅት ውስጥ የተከማቸ የጦር መሣሪያ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የደሴ ከተማ 1ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጥላሁን ፈንታው÷ ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከህብረሰቡ በደረሰ ጥቆማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ቀበሌ ሸርፍ ተራ አካባቢ በአንድ ግለሰብ የንግድ ሱቅ ውስጥ ተከማችቶ የነበረ የተለያየ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተይዟል ብለዋል፡፡

የተያዙት የጦር መሳሪያዎችም÷ 66 የተለያዩ ጥይቶች፣ 11 በምቦች፣ 6 ታጣፊና ሰደፍ ክላሽንኮቭ እንዲሁም በተለምዶ “አብራራው” ተብለው የሚጠሩ 2 ጠብመንጃዎች እና 1 ሽጉጥ መሆናቸውን ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ግለሰቡ የተለያየ ሸቀጣሸቀጥ ለመሸጥ የንግድ ፈቃድ ያለው ቢሆንም÷ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በማከማቸት ለጥፋት ዓላማ ሊያውል ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቁመው ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን አብራርተዋል፡፡
ህብረተሰቡ ላሳየው ትብብር ምስጋና ያቀረቡትምክትል ኢንስፔክተር ጥላሁን ፈንታው÷ በቀጣይም ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የጥፋት ኃይሎች ያሰቡት የሽብር ተግባርም ሆነ ማንኛውንም ሕገ ወጥ ተግባር እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.