Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2014 የውድድር ዓመት አንደኛው ዙር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2014 የውድድር ዓመት አንደኛው ዙር የውድድር መርሐ ግብር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
መርሐ ግብሩ መቋጫውን ያገኘው÷ መከላከያ ጌዲኦ ዲላን 6 ለ 1 እንዲሁም ቦሌ ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊትን 3 ለ 1 ያሸነፉበትን የ13ኛ ሣምንት ጨዋታዎች መካሄድ ተከትሎ ነው፡፡
የደረጃ ሠንጠረዡን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ32 ነጥብ እየመራ ሲሆን÷ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ28 እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ በ26 ነጥብ ይከተላሉ፡፡
የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን÷ ሎዛ አበራ በ21 ጎል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትመራ÷ ንግስት በቀለ በ12 ጎል ከቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም ሴናፍ ዋቁማ ከመከላከያ በ12 ጎል ይከተላሉ፡፡
የአንደኛውን ዙር የውድድር መርሐ ግብር መጠናቀቅ ተከትሎም÷ ሁለተኛው ዙር ውድድር ከግንቦት 14 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ የእግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.