ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ማስወንጨፏ ተሰማ፡፡
የአሁኑ የሚሳኤል ሙከራ የሃገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሃገራቸውን የኒውክሌር የጦር መሳሪያ አቅም በማሳደግ በጠላቶቻችን ላይ እንጠቀማለን ካሉ ከቀናት በኋላ የተደረገ ነው።
የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ አዛዦች በሰጡት መግለጫ ሚሳኤሉ ከሰሜን ኮርሪ ዋና ከተማ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ መተኮሱን አረጋግጠዋል።
በመግለጫቸው ተጨማሪ የሚሳኤል ሙከራዎች መኖሩን እየተከታተልን ነው ማለታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል።
ሰሜን ኮሪያ በዚህ አመት እያደረገች ያለው ያልተለመደ እና ተደጋጋሚ የጦር መሳሪያ ሙከራ የኒውክሌር መሳሪያ አቅሟን ለማዘመን እና በኒውክሌር ድርድሩ በዋሺንግተን ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ይነገራል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡