Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ተፎካካሪ ፖርቲዎች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ የተፎካካሪ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በሀገራዊ ምክክር ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ የተፎካካሪ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አበበ÷ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚያግባቡ ጉዳዮችን ለመለዋወጥ አመቺ ይሆናል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከንቲባዋ የህዝብ ግንኙነት ዋና አማካሪ አቶ አለማየሁ እጅጉ÷ ከመገፋፋትና ከጥላቻ እርቀን አማራጭ ሀሳቦችን አማራጭ ለሌላት ሀገራችን የተለዩ እና ለሀገር የሚበጁ ሀሳቦችን በውይይት አዳብሮ መጓዝ አሽፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
በውይይቱ ላይ ሀገራዊ ምክክር እና የሀገራት ተሞክሮን የሚያሳዩ ሰነዶች ቀርበው በተሳታፊዎችሳይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.