Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሊያ ታደሰ የጊኒ ዎርም በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ላይ ምልከታ ለማድረግ ጋምቤላ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጊኒ ዎርም በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ምልከታ ለማድረግ ጋምቤላ ክልል ገቡ፡፡
ሚኒስትሯ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዶክተር ሊያ በሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የጊኒ ዎርም ስርጭት በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው በጎግ እና አቦቦ ወረዳ የመስክ ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የጊኒ ዎርም በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቅሷል፡፡
በመስክ ምልከታው ላይ የጤና ሚኒስትዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ የክልል፣ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ ከጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.