የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችን የሚዘክር የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፈተ

By Meseret Awoke

May 04, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችን የሚዘክር የፎቶ አውደ ርዕይ በብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጽሐፍት ተከፈተ፡፡

በአውደ ርዕዩ ከአድዋ ድል በኋላ የነበሩ ታሪኮችን የሚያሳዩ ፎቶዎች፣ ደብዳቤዎችና የአርበኞች ፎቶዎችም ለእይታ ቀርበዋል።

ይህ አውደ ርዕይ ጀግኖች አርበኞች ሃገርን ለማስቀጠል የከፈሉትን ዋጋና በአንድነት መሻገር የማይቻል ችግር እንደሌለ ለትውልዱ ለማስተማር አላማው ያደረገ ነው። የጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፥ ጀግኖች አርበኞች ዋጋ ከፍለው ሃገር እንዳስቀጠሉ ሁሉ የአሁኑ ትውልድም ከአርበኞች አንድነትን፣ ፍቅርንና መቻቻልን ተምሮ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአንድነት ሊሻገር ይገባል ብለዋል።

በነገው እለት በሚከበረው 81ኛው የአርበኞች ቀንም ከ50 አመት በኋላ የመከላከያ ሰራዊት ተገኝቶ አበባ እንደሚያስቀምጥ ልጅ ዳኒኤል ጆቴ ተናግረዋል።

የፎቶ አውደ ርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 28 ቀን ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡