Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካው ዓለም አቀፍ የማዕድን ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የማእድን ሀብቷን በስፋት ለማስተዋወቅ ዝግጅት መጠናቀቋ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የማዕድን ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን በሰፊው ለማስተዋወቅ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ኢንጂነር ታከለ ዑማ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ በማህባራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳስታወቁት ፥ ከቀናት በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው “Investing in African Mining ( INDABA )” የማዕድን ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን በሰፊው ለማስተዋወቅ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ጉባዔው በአፍሪካ ማዕድንን ካፒታላይዜሽን እና ልማት ላይ ያተኮረ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ትልቁ የማዕድን ኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ እንደሆነ ይነገርለታል።

ጉባዔው ለኢንዱስትሪው የወደፊት እርምጃ ጉልህ አስተዋጽዖ እንዳለው የሚጠቀስ ሲሆን፥ አዳዲስ ስልቶችን፣ ወሳኝ ውይይቶችን እና ስምምነቶችን የሚፈፀሙበት ነው።

ሚኒስትሩ፥ በዛሬው ዕለት ከአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኔብሌት ጋር በጉባኤው ላይ በተናጠል የአውስትራሊያ የማዕድን ኩባንያዎች የውይይት መድረክ ለመዘጋጀት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ በሰፊው በማእድን የወጪ ንግድን፣ በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ማዕድናት እንዲሁም የኃይል ማዕድናትን በማስተዋወቅ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድን ለማሳከት ግዙፍ የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለመሳብ እንደምትሰራም ነው አክለው የገለጹት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.