የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ አማረ ሰጤን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ መልካሙ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎች የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በነፋስ መውጫ ከተማ እየተሰሩ እና እየተገነቡ የሚገኙ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች የመንገድ ኮብልስቶን ንጣፍ፣ ደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ እያስገነባው የሚገኘውን ካምፓስ እና ሌሎችን በርካታ መሰረተ ልማቶች እና ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
የነፋስ መውጫ ከተማ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ተይዛ የነበረች ከተማ ስትሆን÷ በሽብር ቡድኑ የወደሙ ተቋማትን እና የተዘረፉ ንብረቶችን በመተካት በመንግስት በጀት እና በልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል፡፡
በግንባታ ላይ ከሚገኙ መሰረተ ልማቶች እና ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የመሰረት ድንጋዮችም መቀመጣቸውን ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በዛሬው ዕለት አዶኒያ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እና የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር የቢሮ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በዕለቱ የክብር እንግዶች ተቀምጧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡