Fana: At a Speed of Life!

ሞስኮ ዩክሬን ከምዕራባውያን ያገኘቻቸውን የጦር መሳሪያ የምታጓጓዝባቸው ናቸው ያለቻቸውን የባቡር መስመሮች ከስራ ውጪ ማድረጓን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ሞስኮ ዩክሬን ከምዕራባውያን ያገኘቻቸውን የጦር መሳሪያ የምታጓጓዝባቸው ናቸው ያለቻቸውን ስድስት የባቡር መስመሮች የሀይል ጣቢያዎች በማውደም ከስራ ውጪ ማድረጓን ገለፀች።

በድብደባው አራት የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን ጨምሮ 40 የዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ነው የተባለው።

በተለይ የባቡር መስመሮቹ ምን ዓይነት ምዕራባውያን ሰራሽ የጦር መሣሪያዎችን ሲያጓጉዝ እንደነበር ግልፅ አልተደረገም።

የባቡር ሀይል ጣቢያዎቹ ከባህርና ከዓየር በተተኮሱ መሣሪያዎች እንዲወድሙ መደረጉን ሚኒስቴሩ መግለፁን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.