ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሞስኮ ዩክሬን ከምዕራባውያን ያገኘቻቸውን የጦር መሳሪያ የምታጓጓዝባቸው ናቸው ያለቻቸውን የባቡር መስመሮች ከስራ ውጪ ማድረጓን ገለፀች

By Feven Bishaw

May 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ሞስኮ ዩክሬን ከምዕራባውያን ያገኘቻቸውን የጦር መሳሪያ የምታጓጓዝባቸው ናቸው ያለቻቸውን ስድስት የባቡር መስመሮች የሀይል ጣቢያዎች በማውደም ከስራ ውጪ ማድረጓን ገለፀች።

በድብደባው አራት የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን ጨምሮ 40 የዩክሬን ወታደራዊ ኢላማዎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ነው የተባለው።