Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጨማሪ በጀትና ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጨማሪ በጀትና ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች የ19 ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

የልሉ ምክር ቤት 874 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን፥ በጀቱ የውስጥ ገቢን በማሻሻል የሚመነጭ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባከናወነው 6ኛ ዙር 1ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ መንግሥት አስፈፃሚ አካላት የ9 ወራት ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ቀርቦ የምክር ቤት አባላት ሃሳብ፣ አስተያየቶችን እንዲሁም ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
የተነሱ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ሰፊ ማብራሪያ እና ምላሾች ከተሰጡ በኋላ ምክር ቤቱ ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

በበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አማካይነት ለክልሉ ምክር ቤት የበጀት ዕቅድ ማሻሻያ ቀርቦም ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ መሆኑን ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱላቻ አማካይነት ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ለወረዳ ፍርድ ቤቶች የ19 ዳኞችን የሹመት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፥ በቀረቡ ዳኞች ላይ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ውይይት በማድረግ የዳኞቹ ሹመት ፀድቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.