Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ የመኸር ዘመን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሄክታር መሬት ለማረስ መታቀዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2014/2015 የመኸር ዘመን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሄክታር መሬት ለማረስ መታቀዱን የክልሉ ግብና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ክልል አቀፍ የመኸር እርሻ ንቅናቄ መድረክ በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በክልላዊ በ2014/2015 የመኸር እርሻ ንቅናቄ መድረኩ የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ፥ ባለፉት ዓመታት ክልሉ በገጠመው የጸጥታ ችገር ያለማን መሬት በማካካስ በምርት ዘመኑ 1 ሚሊየን 119 ሺህ 840 ሄክታር ለማልማት ግብ ተጥሏል ብለዋል፡፡

በክልሉ በመኸር እርሻ ሊለማ የታቀደው መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለምቶ የታለመው 34 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት እንዲመረት የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች አርሶ አደሩ ጉልበቱን ጊዜውንና መሬቱን ተጠቅሞ የባለፉት የእርሻ ዘመን የታጣውን ምርት ማካካስ እንዲቻል ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መግባት እንዳለበት ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡

በተለይ እንደ ሀገር የምግብ እህል ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለኤክስፖርት የሚውሉ ትርፍ ምርት ለማምረት ለታቀደው እቅድ ስኬት አርሶ አደሩና ኢንቨስተሩ ያሉ አመራጮችን ተጠቅሞ የእርሻ መሬቱን በማልማት ጾም የሚያድር መሬት እንዳይኖር ባለሙያውና ባለድርሻ አካላት ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡

በመድረኩም የሰብል ልማትና ጥበቃ፣ ቴክኖሎጅ እንዲሁም የሜካናይዜሽኝ እርሻን በክልሉ ለማስፋፋት የታቀዱ ዝርዝር ተግበራት የሚያስዳስስ የንቅናቄ ሰነዶች መቅረባቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገነነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በቀረቡ ሰነዶች እንደተገለጸው ፥ በክልሉ በምርት ዘመኑ የሚጠብቀውን ውጤት ለማስመዝገብ ምርታማነትን ሊያሻሽሉ የሚችሉ አዳዲስ የተሻሻሉ አስራሮችና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ የታሳተፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ፥ በቀጣይ 2014/2015 የመኸር እርሻ በተሻለ መልኩ ወደ ስራ ለመግባት የአርሶ አደሩ የአስተራረስ ዘዴን በማሻሻል ጉልበትና ጊዜን በሚቆጥብ በመልኩ ወደ ስራ እንዲገባ የምርጥ ዘርና የግብዓት አቅርቦት እንዲሁም በሜካናይዜሽን እርሻ እንዲሳተፉም የትራክተር አቅርቦትና የነዳጅ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ አርሶ አደሮችም ሆኑ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች ያላቸውን መሬት እንዲያለሙ ከክልል እስከ ወረዳ የተቀናጀ ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በአሶሳ ዞን ከወርቅ ቁፋሮ እና ከመሬት ኪራይ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለይቶ መፍታት እንደሚሻም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.