በአፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የተመራ የኢትዮጵያ ልኡክ በጅቡቲ ጉብኝት አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የኢትዮጵያ ልኡክ በጅቡቲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረገ።
የኢትዮጵያ ልኡክ በጅቡቲ ጉብኝቱን ያደረገው በሀገሪቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሃመድ አሊ ሁመድ በቀረበለት ግብዣ ነው።
በዚህም አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በጅቡቲ ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን፥ በንግግራቸውም በሁሉቱ ሀገራት መካከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፍ ያለውን ግንኙነት አንስተዋል
የኢትዮጵያ መንግስትም የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናከር አፈ ጉባኤው አረጋግጠዋል።
የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የጅቡቲ ምክር ቤት ትብብር ወደፊትም የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም አስታውቀዋል።
በአፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የሚመራ የኢትዮጵያ ልኡክ በሀገሪቱ ቆይታው በጅቡቲ ወደብ ያለውን የስራ እንቅስቃሴም ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በተጨማሪም ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የማዳበሪያ የማጓጓዝ ስራንም ስፍራው ድረስ በመሄድ ተመልክተዋል።