Fana: At a Speed of Life!

ዐርበኝነት ማለት በሀገር ጉዳይ ላይ ለእውነትና ለእምነት የሚከፈል መሥዋዕትነት ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዐርበኝነት ማለት በሀገር ጉዳይ ላይ ለእውነትና ለእምነት የሚከፈል መሥዋዕትነት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 81ኛ ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል ቀንን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የሀገራቸውን ነጻነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲሉ ምትክ የሌለውን ሕይወታቸውን መክፈላቸውን አስታውሰዋል።

ዛሬ ይሄንን የሕይወት ዋጋ የከፈሉትን ዐርበኞቻችንን በክብር እናስባቸዋለን ነው ያሉት።

እኛም ልጆቻቸው፣ ቀደምት ዐርበኞች ላከበሯት ሀገራችን ልዕልናና ብልጽግና ለማጎናጸፍ ዋጋ የምንከፍል ተተኪ ዐርበኞች መሆናችንን ልናረጋግጥ ይገባናልም ብለዋል በመልዕክታቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.