Fana: At a Speed of Life!

አርበኞቻችን እንዳሳዩን የድል ሚስጥሩ ጀግንነት እና እንደ ሀገር አብሮ መቆም ነው – ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርበኞቻችን እንዳሳዩን የድል ሚስጥሩ ጀግንነት እና እንደ ሀገር አብሮ መቆም ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንቷ በ81ኛው የአርበኞች የድል በዓል ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ መደጋገፍ እና አብሮ መቆምን ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ሁሉ መነጋገር ፣ መግባባት እና አቅጣጫችንን አስተካክለን መራመድ ይኖርብናልም ነው ያሉት፡፡
ጀግኖችን ስንዘክር ሌሎችን በርካታ ጀግኖች ሀገራችን እንድታፈራ ቆርጠን እንደምንሰራ ማረጋገጥ አለብንም ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሀውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡
በአንድነት ከመቆም ውጭ ሌላ ምርጫ የለንም ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷ የአሁኑ ትውልድ የጥንት አባቶቹን የጀግንነት ታሪክ በሁሉም መስክ መድገም እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
የጥንታዊ ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በመርሐ ግብሩ ባደረጉት ንግግር÷ የአሁኑ ትውልድ ስለአገር አንድነት መስራት አለበት ብለዋል፡፡
ለአገር አንድነት በፍቅር በመተሳሰብ ችግሮችን በመነጋገር እና በምክክር በመፍታት አገርን ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በሻምበል ምህረት
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.