Fana: At a Speed of Life!

የጤና ባለሙያዎች መከላከያ ሰራዊቱ በሁለት እግሩ እንዲቆም የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል – ጀነራል አበባው ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የጤና ባለሙያዎች የአገር መከላከያ ሰራዊት በሁለት እግሩ እንዲቆም የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል” ሲሉ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ተናገሩ፡፡
በሕግ ማስከበርና በኅብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻ የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎችና ተቋማት በአማራ ክልል የጤና ቢሮ አስተባባሪነት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ÷ “በዘመቻው ወቅት የነበረውን ጉዳት ከጤና ባለሙያው በላይ የሚረዳ የለም”፤ የጤና ባለሙያዎቹ በጦርነቱ የተጎዱ የሰራዊት አባላትን በማከምና በማገልገል ሙያዊና አገራዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ብለዋል፡፡
ባለሙያዎቹ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ለሙያቸው ታማኝ ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አድናቆትና ክብር እንዳለውም ጀነራል አበባው ገልጸዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማህበራዊ ዘርፍ አስትባባሪ አቶ ስዩም መኮንን በበኩላቸው÷ የጤና ባለሙያዎቹ ከመከላከያ ሰራዊቱ ባልተናነሰ እስከ ሕይወት መስዋትነት በመክፈል ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.