Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከዛሬ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል ፡፡

የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን÷ ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በዚሁ ዓመት ጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን ÷ አሁን የሚሰጠው ክትባት የዚሁ ክትባት አንዱ አካልና ሁለተኛው ዙር መሆኑ ታውቋል፡፡
በመሆኑም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ህጻናትን በማስከትብ ከሚደርስባችው የአካል ጉዳትና የጤና ችግር በመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
555ሺህ 9 የሚሆኑ ህጻናትን ለመከተብ መታቀዱም ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.