Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ወጣቶች ህብረት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የምርጥ ዘር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ወጣቶች ህብረት በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የምርጥ ዘር ድጋፍ አደረገ፡፡

በክልሉ ድርቅ በተከሰተባቸዉ 7 ዞኖች የበልግ ዝናብ መጣል መጀመሩን ተከትሎ አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ወደ ግብርና ስራቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ድጋፉ እንደተደረገ የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር ፅ/ቤት ሀላፊ ወጣት ገዛኸኝ አንዳርጌ ተናግሯል፡፡

ሁለት መቶ ብር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን በሚል መሪ ቃል የክልሉን ወጣቶች ከቀበሌ እስከ ክልል በማሳተፍ ከ17 ሚሊዮን 216 ሺህ ብር በላይ በመሰብሰብ በድርቅ የተጎዱ ዜጎች ወደ ወደበኛ ስራቸዉ እንዲመለሱ ድጋፍ አድርገናል ነው ያለው፡፡

ድርቁ ለከፋባቸዉ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ እንዲሁም ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች 3442 ኩንታል የስንድ ምርጥ ዘር ከኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት ገዝተኝ እንዲደርሳቸዉ አስረክበናልም ብሏል፡፡

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ የበል ወቅት ተከትሎ በክልሉ ወጣቶች ህብረት የተደረገዉ የምርጥ ዘር እርታዳ በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም እተሰሩ ያሉ ስራዎችን እንደሚያቀላጥፍ ገልፀዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮም ድርቅ በተከሰተባቸዉ 7 ዞኖች እየጣለ የሚገኘዉን የበለግ ዝናብ በድርቅ አደጋዉ የተጎዱ ዜጎች እንዲጠቀሙ ለማድረግ ከምርጥ ዘር ድጋፍ በተጨማሪ ከ15 ሺህ በላይ ኩንታል ማዳበሪያ እንዲደርሳቸዉ ማድረጉን ነዉ የተናገሩት፡፡

በዞኖቹ ከብቶቻቸዉ አልቀዉባቸዉ መሬታቸዉን ማረስ ያልቻሉ ሁሉም አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ዉስጥ ተካተዉ እንዲያመርቱ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.