የሀገር ውስጥ ዜና

በአብርሆት ቤተመጻሕፍት ለአንድ ወር የሚቆይ መፃህፍት የማሰባሰብ መርሀ ግብር ተጀመረ

By Meseret Awoke

May 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘’ሚሊዮን መፃህፍት ለሚሊዮን ትውልድ’’ በሚል በአብርሆት ቤተመጻሕፍት ለአንድ ወር የሚቆይ መፃህፍት የማሰባሰብ መርሀ ግብር ተጀመረ።

ለቤተመጻሕፍቱ ሁሉም አሻራውን እንዲያሳርፍ የተዘጋጀውን መርሃ ግብር ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በይፋ አስጀምረውታል።

ፕሬዚዳንቷ ፥ ቤተመጻሕፍት የሰውልጅ ዕውቀት የሚሸምትበት ፤ አስተሳሰብ የሚቀረፅበት ቦታ እንደመሆኑ ዛሬ የተጀመረው መርሃ ግብር መስጠትን ባህል አድርጎ ለሌሎች በእውቀት እንድንተርፍ ያስችላል ብለዋል።

የተጀመረው መርሃ ግብር በየቤቱ የተቀመጡ መፅሃፍቶች በማሰባሰብ መጪዋን ኢትዮጵያ የእውቀት ድልድይ ሆኖ ለመገንባት ዓላማ ማድረጉን የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፋ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ገልፀዋል።

ዛሬ በተጀመረዉ መርሃ ግብር ጉምሩክ ኮሚሽን ከ150ሺህ መፃህፍት በላይ እንዲሁም የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር 5ሺህ መፃህፍትን አስረክበዋል።

በሜሮን ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡