Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው የአፍሪካ ሀገራት ቁጥር 6 ደርሷል

አዲስ አበባ ፣የካቲት 24፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሀገራት ቁጥር ስድስት መድረሱ ተገልጿል።

በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት በመዛመት ላይ ይገኛል።

አሁን ላይም ቫይረሱ ከ70 በላይ በሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ መስፋፋቱን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

በዚህ መሰረትም በአፍሪካ ከናይጄሪያ፣ ግብጽ እና አልጄሪያ በተጨማሪ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ እና ሴኔጋል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሌሎች ሀገራት መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ከ 3ሺህ 100 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ90 ሺህ በላይ ሆኗል።

ከዚህ ውስጥ በቻይና ብቻ እስካሁን 80 ሺህ 151 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥2 ሽህ 943 ዜጎችደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል።

በቫይረሱ ከቻይና ቀጥለው በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ ሀገራት ኢራን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ጣሊያን  መሆናቸው  በዘገባው  ተመላክቷል።

ምንጭ፥ ቢቢሲ እና ሲ ቢ ኤስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.