Fana: At a Speed of Life!

983 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 983 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተገለፀ፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ህጻናት ሲሆኑ 969ኙ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ 18 ሺህ 900 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.