Fana: At a Speed of Life!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ45 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ45 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እንዳሉት ፥ የክልሉን ስራ አመራር ተቋም የክልሉን አመራርና ፈጻሚውን በማብቃት የክልሉ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም ተቋሙ በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ የአመራር ማስልጠኛ አካዳሚ እንዲሆን ከ800 በላይ ህዝብ መያዝ የሚችል ዘመናዊ መስብሰቢያ አዳራሽ በ45 ሚሊየን ብር ለማስገንባት የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ ማኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ በጀት ዓመትም የተሻለ የክልሉ የአመራር ማስልጠኛ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል የተጀመሩ ግንባታዎችን እንዲጠናቀቁ ከማድረግ ባለፈ በቁስቁስ፣ በባለሙያና በቴክኖሎጂ እንዲደራጅ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል ርዕስ መስተዳድሩ፡፡

የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር እና የክልሉ ስራ አመራር ማስልጠኛ ተቋም የቦርድ ሰብሳቢ መሀመድ አብዱልአዚዝ በበኩላቸው ፥ ተቋሙን ማዘመን አመራሩና ፈጻሚውን ወጤታማ ስራዎችን እንዲተገበሩ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙን ለማዘመን እንደቦርድ ወይይት በማድረግ በቅድሚያ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገነባ በመወሰን ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል የቦርድ ሰብሳቢው፡፡

በተለይ ተቋሙን በማዘመን ለሰልጣኝ እና ለአሰልጣኖች ምቹ እንዲሆን ሊሟሉ የሚገቡ መሰረታዊ ጉዳዮች በጥናት ተለይተዋል ያሉት የቦርድ ሰብሳቢው ፥ የውስጥ ገቢው እንዲጠናከርም የመንግስት ተቋማት የሚሰጧቸው አጫጭር ስልጠናዎችን በተቋሙ እንዲሰጡ ለማስቻል ጥረቶች መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ርዕስ መስተዳድር የግንባታ ማስጀመሪያ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ45 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገናባ ሲሆን ፥ በ741 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍና በሁለት ዓመታት ወስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.