Fana: At a Speed of Life!

በሰሉልታ ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሱሉልታ ከተማ ንጋት አስር ሰአት አከባቢ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
በተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ቢደርስም በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የከተማዋ ፖሊስ ገልጿል።
አደጋው ነዳጅ በበርሜል ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ሲያደርግ ከነበረ መኪና በተፈጠረ እሳት የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ነገሪ ዲባ፥ በአደጋው አንድ ሆቴልና የተለያዩ ሱቆች ከእነ መሉ ንብረታቸው ወድመዋል ብለዋል።
የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ እየተጣራ እንደሆነም ኮማንደሩ ገልፀዋል::
አደጋው ወደተለያዩ አካባቢዎች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ከአዲስ አበባ ከተማ በተላከ የእሳትና ድንገተኛ መከላከከያ ቡድን በቁጥጥር ስር መዋሉን ኦቢኤን ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.