Fana: At a Speed of Life!

በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የዳያስፖራው ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የዳያስፖራው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ዳያስፖራዎች በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ ያለመውን ይህን ውይይት÷ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ አገልግሎት ከሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ ኢድሪስ፥ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ዳያስፖራዎች በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል።
ዳያስፖራዎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዘርፎች ተሳትፏቸውን በማሳደግ በሀገር ግንባታ ላይ ገንቢ ሚና ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።
በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው መሆኑን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
በውይይቱ ላይ የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ ዳያስፖራዎች፣ ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ነው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.