Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ዣንጥራር አባይ የተመራ ልዑክ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የጓሮ አትክልትና የመሰረተ ልማት ስራን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ የተመራ የአመራሮች ልዑክ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እየተሰራ ያለውን የጓሮ አትክልትና የመሰረተ ልማት ስራ ጎበኘ፡፡

ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በክፍለ ከተማው እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ያሉበትን ሁኔታና የጓሮ አትክልት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም በርካታ ተስፋ ሰጭ ጅምሮች መመልከታቸውን የገለፁት አቶ ዣንጥራር÷ በተለይ የጓሮ አትክልት ስራው በስፋት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይ የአስፋው ሜዳ ግንባታ እና በወረዳ 14 የሚገኘው የጤና ጣቢያ ግንባታ መጎብኘታቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.