Fana: At a Speed of Life!

የሪፐብሊኩ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪፐብሊኩ የቀድሞ ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሌተናል ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ በ81 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቻቸው ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

ቤተሰቦቻቸው እንደገለፁት ኮሎኔል ፍስኃ የልብ ሕመም የነበረባቸው ሲሆን፥ ህክምናቸውን በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ሲከታተሉ ቆይተዋል።

የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሐረር ጦር አካዳሚ 3ኛ ኮርስ ምሩቅ መኮንን የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ፥ በደርግ ዘመን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

በመጨረሻም የሪፐብሊኩ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው የሚታወስ ነው።

ከደርግ ውድቀት በኋላም 20 አመታትን በእስር አሳልፈዋል።

የህግ ምሩቅ የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ፍስኃ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” መጽሀፍ ደራሲም ናቸው።

የቀብር ስነ ስርዓታቸውም በነገው እለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ተገልጿል።

ሌተናል ኮሎኔል ኮሎኔል ፍስኃ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበሩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.