Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ከመጡ የዳያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ከመጡ የዳያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ።

አቶ ደመቀ የተወያዩት “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪ ከእንግሊዝ ሀገር ከመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ሲል ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.