የሀገር ውስጥ ዜና

አየር ኃይል የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት በሚችልበት የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል – ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

By Meseret Awoke

May 07, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የመስክ ምልከታ አደረገ።

በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በዶክተር ዲማ ነገዎ ለተመራው ልዑክ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እና የአየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ባደረጉት ገለፃ ፥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎች በአቪዬሽን፣ በአየር መከላከል፣ በሰው ኃይል አቅም እና በመሰረተ ልማት ግንባታ ስኬት ተመዝግቧል።

አየር ኃይል በአሁኑ ወቅት በሁሉም ረገድ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት በሚችልበት የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዋና አዛዡ ተናግረዋል።

በመስክ ምልከታቸው አየር ኃይል ህዝብና መንግስት የጣሉበትን አደራ በቁርጠኝነት እየተወጣ መሆኑን የገለፁት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ ተቋሙ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና ሊቸረው ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡